عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إِذَا مَرِضَ الْعَبْدُ أَوْ سَافَرَ كُتِبَ لَهُ مِثْلُ مَا كَانَ يَعْمَلُ مُقِيمًا صَحِيحًا».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 2996]
المزيــد ...
አቢ ሙሳ አል-አሽዓሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2996]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ስለአሏህ እዝነትና ችሮታ እየነገሩን ነው። ይህም አንድ ሙስሊም በሀገሩ እና ጤነኛ ሳለ ልምድ ያደረገው መልካም ስራ ከዚያም ዑዝር ገጥሞት ታሞ ማድረግ ባይችል፣ ወይም በጉዞ ወይም ደግሞ በሌላ በየትኛውም ትክክለኛ ምክንያት ሳያደርገው ቢቀር ልክ ጤነኛና በሀገሩ ሆኖ ሲያደርግ እንደነበረው ምንዳ ሙሉ ሆኖ ይጻፍለታል።