عَن أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيَّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا وُضِعَتِ الجِنَازَةُ وَاحْتَمَلَهَا الرِّجَالُ عَلَى أَعْنَاقِهِمْ فَإِنْ كَانَتْ صَالِحَةً قَالَتْ: قَدِّمُونِي، وَإِنْ كَانَتْ غَيْرَ صَالِحَةٍ قَالَتْ: يَا وَيْلَهَا أَيْنَ يَذْهَبُونَ بِهَا؟ يَسْمَعُ صَوْتَهَا كُلُّ شَيْءٍ إِلَّا الإِنْسَانَ، وَلَوْ سَمِعَهُ صَعِقَ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1314]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድምጿን ይሰማል። የሰው ልጅ ቢሰማው ኖሮ ራሱን ስቶ ይወድቅ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1314]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀናዛ ቃሬዛ ላይ የተቀመጠ ጊዜና ሰዎችም ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ መልካም ከሆነች ከፊት ለፊቷ ፀጋዎችን ስለምትመለከት "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ ከፊት ለፊቷ ቅጣትን ስለምትመለከት በሚያወግዝ ድምፅ "ወይ ጥፋቷ! የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?!" ትላለች። ከሰው በቀር ሁሉ ነገር ድምጿን ይሰማታል። ሰው ቢሰማው ኖሮ የሚሰማው ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ራሱን ይስት ነበር አሉ።