عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
جَاءَ رَجُلٌ إِلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، أَرَأَيْتَ إِنْ جَاءَ رَجُلٌ يُرِيدُ أَخْذَ مَالِي؟ قَالَ: «فَلَا تُعْطِهِ مَالَكَ» قَالَ: أَرَأَيْتَ إِنْ قَاتَلَنِي؟ قَالَ: «قَاتِلْهُ» قَالَ: أَرَأَيْتَ إِنْ قَتَلَنِي؟ قَالَ: «فَأَنْتَ شَهِيدٌ»، قَالَ: أَرَأَيْتَ إِنْ قَتَلْتُهُ؟ قَالَ: «هُوَ فِي النَّارِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 140]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
«አንድ ሰውዬ ወደ አላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን እንዳትሰጠው" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱም "ቢገለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተ ሰማዕት ነህ።" አሉት። እርሱም "ብገለውስ?" አላቸው። እርሳቸውም "እርሱ እሳት ውስጥ ነው።" አሉት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 140]
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እስኪ ንገሩኝ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን መስጠት አይጠበቅብህም" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱም "እርሱ ቢገለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተ ሰማዕት ነህ።" አሉት። እርሱም "እኔ ብገለውስ?" አላቸው። እርሳቸውም "እርሱ የትንሳኤ ቀን በእሳት ውስጥ ለመቀጣት የተገባ ነው።" አሉት።