عَنْ سَمُرَةَ بْنِ جُنْدَبٍ وَالْمُغِيرَةِ بْنِ شُعْبَةَ رضي الله عنهما قَالَا: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ حَدَّثَ عَنِّي بِحَدِيثٍ يُرَى أَنَّهُ كَذِبٌ، فَهُوَ أَحَدُ الْكَاذِبِينَ».
[صحيح] - [رواه مسلم في مقدمته]
المزيــد ...
ከሰሙራ ቢን ጁንዱብና ሙጚራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ውሸት መሆኑን እያወቀ ከኔ አንድ ሐዲሥን ያወራ ሰው ከውሸታሞች አንዱ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሶሒሕ ሙስሊም]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ እየዋሸ እንደሆነ እያወቀ ወይም እየተጠራጠረ ወይም በአብዛኛው ግምቱ እየዋሸ እንደሆነ እየተሰማው ከርሳቸው ንግግርን ያስተላለፈና ያወራ ሰው ይህንን ውሸት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀጠፈው ጋር (በወንጀሉ) ይጋራል።