عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«نَضَّرَ اللَّهُ امْرَأً سَمِعَ مِنَّا شَيْئًا فَبَلَّغَهُ كَمَا سَمِعَ، فَرُبَّ مُبَلِّغٍ أَوْعَى مِنْ سَامِعٍ».
[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 2657]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2657]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የርሳቸውን ሐዲሥ ሰምቶ ለሌላው እስኪያደርስ ድረስ የሸመደደ ሰው አላህ በዱንያ ውስጥ ውበትን፣ ቁንጅናና ብርሃንን እንዲሰጠው፤ በመጪው አለም ደግሞ ወደ ጀነት ብርሃን፣ ፀጋና ውበት አላህ እንዲያደርሰው ዱዓ አድጉለት። አንዳንዴ ሐዲሥ የሚነገረው ሰው ሐዲሡን መጀመርያ ከሰማው ሰው የበለጠ ሸምዳጅ፣ ተገንዛቢ፣ ከሐዲሡ ፍሬሃሳቦችን መዞ የሚያወጣ ይሆናል። በዚህም የመጀመሪያው ሰውዬ በአስተማማኝ መልኩ መሸምደዱንና "ነቅል" (መውሰድን) ሲችል ሁለተኛው ደግሞ በአስተማማኝ መልኩ መገንዘቡንና መረዳቱን የቻለ ይሆናል።