عن طارق بن أشيم الأشجعي رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ قَالَ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَكَفَرَ بِمَا يُعْبَدُ مِنْ دُونِ اللهِ حَرُمَ مَالُهُ وَدَمُهُ، وَحِسَابُهُ عَلَى اللهِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 23]
المزيــد ...
ከጧሪቅ ቢን አሽየም አልአሽጀዒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ለዋሏል: "የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 23]
በምላሱ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ያለና የመሰከረ ሰው ፤ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደና ከኢስላም ውጪ ካሉ ሁሉ እምነቶች የጠራ ሰው በሙስሊሞች ላይ ገንዘቡና ደሙ እርም ይሆናል። እኛ ውጫዊ ከሆኑ ስራዎቹ በስተቀር መፈላፈል አይፈቀድልንም። በኢስላማዊ ህግጋት ይህንን የሚያስገድድ አስገዳጅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ገንዘቡም እንደማይነጠቅ ደሙም እንደማይፈስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።
የትንሳኤ ቀን ሂሳቡን በበላይነት የሚመራው አሏህ ነው። እውነቱን ከሆነ ይመነዳዋል። ሙናፊቅ ከሆነ ደግሞ ይቀጣዋል።