عَنْ بُسْرِ بْنِ سَعِيدٍ، أَنَّ زَيْدَ بْنَ خَالِدٍ الْجُهَنِيَّ رَضيَ اللهُ عنه، أَرْسَلَهُ إِلَى أَبِي جُهَيْمٍ رَضيَ اللهُ عنه، يَسْأَلُهُ مَاذَا سَمِعَ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي الْمَارِّ بَيْنَ يَدَيِ الْمُصَلِّي؟ قَالَ أَبُو جُهَيْمٍ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَوْ يَعْلَمُ الْمَارُّ بَيْنَ يَدَيِ الْمُصَلِّي مَاذَا عَلَيْهِ لَكَانَ أَنْ يَقِفَ أَرْبَعِينَ خَيْرًا لَهُ مِنْ أَنْ يَمُرَّ بَيْنَ يَدَيْهِ» قَالَ أَبُو النَّضْرِ: لَا أَدْرِي قَالَ: أَرْبَعِينَ يَوْمًا أَوْ شَهْرًا أَوْ سَنَةً؟
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 507]
المزيــد ...
ከቡስር ቢን ሰዒድ እንደተላለፈው: ዘይድ ቢን ኻሊድ አልጁሃኒይ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- ቡስር ቢን ሰዒድን ወደ አቡ ጁሃይም -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- በሰጋጅ ፊት ስለማለፍ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምን እንደሰማ ሊጠይቀው ላከው። አቡ ጁሃይምም እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል:
"በሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው በርሱ ላይ ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ በሰጋጅ ፊት ከማለፍ ይልቅ አርባ መቆም ለርሱ መልካም ይሆንለት ነበር።" አቡ ነድር እንዲህ ብሏል" አርባ ሲል አርባ ቀን ወይም ወር ወይም ዓመት እንደሆነ አላውቅም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 507]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ግዴታም ይሁን ሱና ሶላት በሚሰግድ ሰው ፊት ከማለፍ አስጠነቀቁ። ሆን ብሎ ይህንን የሚፈፅም ሰው የሚኖርበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ አርባ መቆምን ይመርጥ ነበር። በሰጋጅ ፊት ከሚያልፍ ይልቅ ይህ ይሻለው ነበር። ይህንን ሐዲሥ ያወራው አቡ ነድር እንዲህ አለ: አርባ ቀን ነው ወይስ ወር ወይስ አመት የሚለውን አላውቅም።