عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي النِّدَاءِ وَالصَّفِّ الْأَوَّلِ ثُمَّ لَمْ يَجِدُوا إِلَّا أَنْ يَسْتَهِمُوا عَلَيْهِ لَاسْتَهَمُوا، وَلَوْ يَعْلَمُونَ مَا فِي التَّهْجِيرِ لَاسْتَبَقُوا إِلَيْهِ، وَلَوْ يَعْلَمُونَ مَا فِي الْعَتَمَةِ وَالصُّبْحِ لَأَتَوْهُمَا وَلَوْ حَبْوًا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 437]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። (ወደ መስጊድ) ማልዶ የመሄድን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ለርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። የዒሻና ሱብሒን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳኹም ቢሆን ይመጡ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 437]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ የሚገኘውን ደረጃ፣ መልካምና በረከት ቢያውቁ ኖሮና ከዚያም ለመቀደምና ቅድሚያ ለማግኘት ማነው የሚገባው ለሚለው እጣ መጣጣል ቢጠበቅባቸው ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። ወደ ሶላት በመጀመሪያ ወቅት ቀድሞ የመሄድንም ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ይሽቀዳደሙ ነበር። ወደ ዒሻ ሶላትና ወደ ፈጅር ሶላት መስጂድ የመምጣት ምንዳ መጠኑን ቢያውቁ ኖሮና ወደ መስጂድ መምጣት ቀላል ባይሆንላቸው ኖሮ ህፃን ልጅ እየዳኸ እንደሚመጣው በጉልበታቸው እየዳኹም ይመጡ ነበር አሉ።