عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مَسْعُودٍ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«تَابِعُوا بَيْنَ الحَجِّ وَالعُمْرَةِ، فَإِنَّهُمَا يَنْفِيَانِ الفَقْرَ وَالذُّنُوبَ كَمَا يَنْفِي الكِيرُ خَبَثَ الحَدِيدِ، وَالذَّهَبِ، وَالفِضَّةِ، وَلَيْسَ لِلْحَجَّةِ الْمَبْرُورَةِ ثَوَابٌ إِلاَّ الجَنَّةُ».
[صحيح] - [رواه الترمذي والنسائي وأحمد] - [سنن الترمذي: 810]
المزيــد ...
ከዓብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር ሌላ ምንም ምንዳ የለውም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን ቲርሚዚ - 810]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሐጅና የዑምራን አምልኮ አቀራርቦ በመፈፀምና ከቻሉ ሳያቆራርጡ በመፈፀም ላይ አነሳሱ። ምክንያቱንም ሲገልፁ ብረትን በወናፍ እሳት መንፋት ብረቱ ላይ የተቀላቀለውን ባዕድ የማዕድን ቆሻሻ ለማስወገድ ምክንያት እንደሆነው ሁሉ እነርሱንም መፈፀም ድህነትንና ወንጀልን እንዲሁም ወንጀል በቀልብ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለማስወገድ ምክንያት መሆናቸውንም ገለፁ።