عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنِينَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا قَالَتْ:
يَا رَسُولَ اللَّهِ، نَرَى الجِهَادَ أَفْضَلَ العَمَلِ، أَفَلاَ نُجَاهِدُ؟ قَالَ: «لَا، لَكُنَّ أَفْضَلُ الجِهَادِ: حَجٌّ مَبْرُورٌ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1520]
المزيــد ...
ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1520]
ሰሐቦች (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) በአላህ መንገድ መታገልንና ጠላቶችን መጋደልን እጅግ በላጭ ከሆኑ ተግባራቶች መካከል እንደሆነ አድርገው ይመለከቱ ነበር። ዓኢሻም (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶችም ጂሃድ ማድረግ ሊፈቀድላቸው ዘንድ ጠየቀች።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሴቶች እጅግ በላጭ የሆነውን ጂሀድ ጠቆሟቸው: እርሱም ቁርኣንና ሐዲሥን የገጠመውና ከወንጀልና ከይዩልኝ የፀዳው ተቀባይነት ያለውን ሐጅ ነው።