+ -

عَنِ العَبَّاسِ بْنِ عَبْدِ الْمُطَّلِبِ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ، عَلِّمْنِي شَيْئًا أَسْأَلُهُ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ. قَالَ: «سَلِ اللَّهَ العَافِيَةَ»، فَمَكَثْتُ أَيَّامًا ثُمَّ جِئْتُ فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ، عَلِّمْنِي شَيْئًا أَسْأَلُهُ اللَّهَ. فَقَالَ لِي: «يَا عَبَّاسُ، يَا عَمَّ رَسُولِ اللهِ، سَلِ اللَّهَ العَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ».

[صحيح لغيره] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 3514]
المزيــد ...

ከዓባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን የምጠይቀው አንዳች ነገር አስተምሩኝ? አልኳቸው። እርሳቸውም "አላህ ደህና እንዲያደርግህ ጠይቀው" አሉኝ። ቀናትን ቆይቼ ከዚያም መጣሁና የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ዐዘ ወጀል የምጠይቀው አንዳች ነገር አስተምሩኝ? አልኳቸው። እርሳቸውም ለኔ "ዐባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! አላህን በዱንያና በመጪው አለም ደህንነትን ጠይቀው።" አሉኝ።»

[በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3514]

ትንታኔ

የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አጎት የሆኑት ዐባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን የሚጠይቁበት ዱዓ እንዲያስተምሯቸው ፈልገው መጡ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ በዲንም፣ በዱንያና በመጪው አለምም ከሚያጋጥሙ መከራና ነውር ደህናና ሰላም እንዲያደርጋቸው እንዲጠይቁ አስተማሯቸው። ዓባስም እንዲህ አሉ: ከቀናት በኋላ በድጋሚ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን የምጠይቅበት አስፈላጊ ዱዓ እንዲያስተምሩኝ ልጠይቅ ተመልሼ መጣሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውዴታን በማሳየት "ዓባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! በዱንያና በመጪው አለም ሁሉንም ጉዳት እንዲከላከልልህና ሁሉንም መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሰጥህ አላህን ደህንነት እንዲሰጥህ ጠይቀው።" አሉት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሁለተኛ ጊዜ ዓባስ ሲጠይቃቸው ተመሳሳይ መልስ መስጠታቸው አንድ ባሪያ ጌታውን ከሚጠይቀው ነገሮች ምርጡ ደህንነት መሆኑን ይጠቁማል።
  2. የዓፊያ (የደህንነት) ትሩፋት መገለፁን እንረዳለን። በዓፊያ ዱንያዊም አኺራዊም ጥቅሞች ይሰበሰባሉና።
  3. ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እውቀትና መልካም ነገር በመጨመር ላይ ያላቸውን ጥረት እንረዳለን።