عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا جَمَعَ اللهُ الْأَوَّلِينَ وَالْآخِرِينَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يُرْفَعُ لِكُلِّ غَادِرٍ لِوَاءٌ، فَقِيلَ: هَذِهِ غَدْرَةُ فُلَانِ بْنِ فُلَانٍ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1735]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1735]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ የትንሳኤ ቀን ለሒሳብ ብሎ የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ ከአላህ ጋር ወይም ከሰዎች ጋር ሊሞላው ቃል የገባውን ቃል ኪዳን ላልሞላ ከዳተኛ ሁሉ ከዳተኝነቱ የሚጋለጥበት አርማ ይተከላል። በዛን እለትም በአርማው ላይ እንዲህ ተብሎ ይለፈፋል: "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የከዳው ክዳት ነው።" ይህም የትንሳኤ ቀን ለተሰበሰቡ ሰዎች መጥፎ ስራውን ለማሳየት ነው።