عن أبي بكرة رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم:
«أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِأَكْبَرِ الْكَبَائِرِ؟» ثَلَاثًا، قَالُوا: بَلَى يَا رَسُولَ اللهِ، قَالَ: «الْإِشْرَاكُ بِاللهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ» وَجَلَسَ وَكَانَ مُتَّكِئًا، فَقَالَ: «أَلَا وَقَوْلُ الزُّورِ»، قَالَ: فَمَا زَالَ يُكَرِّرُهَا حَتَّى قُلْنَا: لَيْتَهُ سَكَتَ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2654]
المزيــد ...
ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦
"'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2654]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለባልደረቦቻቸው እጅግ ትልቅ ስለሆነ ወንጀል ነገሯቸው። እነዚህን ሶስት ወንጀሎችንም ጠቀሱ፦
1 - በአላህ ማጋራት፦ ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፣ ከአላህ ውጪ የሆነን አካል ከአላህ ጋር በተመላኪነቱ ወይ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ እኩል ማድረግ ማለት ነው።
2 - የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፦ ይህም ወላጆች ላይ በንግግርም ይሁን በተግባር በማንኛውም መልኩ ማወክና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው።
3 - ውሸት መናገር ነው። በውሸት መመስከርም እዚህ ውስጥ ይካተታል: ይህም ከተቀጠፈበት አካል ንብረቱን ለመውሰድ ወይም ክብሩ ላይ ወሰን ለማለፍ ወይም የመሳሰሉትን በመፈለግ የተቀጠፈና የተዋሸ ንግግር ሁሉ ማለት ነው።
ከመደጋገማቸው የተነሳ ሶሐቦች ለነቢዩ ካላቸው እዝነትና የሳቸውን መረበሽ ጠልተው ምነው ዝም ባሉ ብለው እስኪመኙ ድረስ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የውሸትን ፀያፍነት እና ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድረውን መጥፎ አሻራ ለማስገንዘብ ከሐሰተኛ ቃል ደጋግመው አስጠነቀቁ።