عَنِ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
أَمَرَنَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِسَبْعٍ، وَنَهَانَا عَنْ سَبْعٍ: أَمَرَنَا بِعِيَادَةِ الْمَرِيضِ، وَاتِّبَاعِ الْجَنَازَةِ، وَتَشْمِيتِ الْعَاطِسِ، وَإِبْرَارِ الْقَسَمِ، أَوِ الْمُقْسِمِ، وَنَصْرِ الْمَظْلُومِ، وَإِجَابَةِ الدَّاعِي، وَإِفْشَاءِ السَّلَامِ، وَنَهَانَا عَنْ خَوَاتِيمَ -أَوْ عَنْ تَخَتُّمٍ- بِالذَّهَبِ، وَعَنْ شُرْبٍ بِالْفِضَّةِ، وَعَنِ الْمَيَاثِرِ، وَعَنِ الْقَسِّيِّ، وَعَنْ لُبْسِ الْحَرِيرِ وَالْإِسْتَبْرَقِ وَالدِّيبَاجِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2066]
المزيــد ...
ከበራእ ቢን ዓዚብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
"የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰባት ነገር አዘዙን፤ ከሰባት ነገርም ከለከሉን። በሽተኛን በመጠየቅ፣ ጀናዛን በመሸኘት፣ ላስነጠሰ ዱዓ በማድረግ፣ መሃላን ወይም የማለን ሰው በማጥራት፣ ተበዳይን በመርዳት፣ የጠራንን ሰው ጥሪውን በማክበር፣ ሰላምታን በማስፋፋት አዘዙን፤ ከወርቅ ቀለበቶች ወይም የወርቅ ቀለበትን ከመልበስ፣ በብር እቃ ከመጠጣት፣ ከሐር የተሰራ ፎጣ ላይ ከመቀመጥ፣ (አልቀስሲይ) ከሐር ክር ተቀላቅሎ የተሰራን ልብስ ከመልበስ፣ ሐርን ከመልበስ፣ ከወፍራም ሐር የተሰራን ከመልበስ፣ ዲባጅ (ውዱን የሐር ጨርቅ) ከመልበስ ከለከሉን።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2066]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊሞችን በሰባት ነገሮች አዘዙ፤ ከሰባት ነገሮችም ከለከሏቸው። ያዘዟቸውም ነገሮች: የመጀመሪያው: በሽተኛን መጠየቅ ነው። ሁለተኛው: ጀናዛን መሸኘት፣ በርሱ ላይ መስገድ፣ መቅበርና ለርሱ ዱዓ ማድረግ ነው። ሶስተኛው: ላስነጠሰና አላህን ላመሰገነ ሰው "የርሐሙከሏህ" በማለት ዱዓ እንዲደረግለት ነው። አራተኛው: የማለን ሰው መሃላውን ማጥራትና ማረጋገጥ ነው። ማለትም በአንድ ጉዳይ ቢማልና አንተ መሃላው እውን እንዲሆን ማድረግ ከቻልክ ለመሃላው ማካካሻ ለማውጣት እንዳይገደድ የማለበትን ጉዳይ ፈፅም ማለት ነው። አምስተኛው: የተበደለን ሰው በማገዝ፣ በተቻለ መጠን በርሱ ላይ የሚደርሰውን በደል በመከላከል መርዳት ነው። ስድስተኛው: እንደሰርግ፣ ዐቂቃና ሌሎችም የምግብ ጥሪዎችን ለጠራ ጥሪውን ማክበር ነው። ሰባተኛው: ሰላምታ መስጠትንና ሰላምታን መመለስ ማስፋፋትና ማሰራጨት ነው። የከለከሏቸው ጉዳዮች ደግሞ: የመጀመሪያው: የወርቅ ቀለበት መልበስና በርሱ መዋብ ነው። ሁለተኛው: በብር እቃ መጠጣት ነው። ሶስተኛው: በፈረስና በግመል ኮርቻ ላይ በሚነጠፍ የሐር ፎጣ ላይ መቀመጥ ነው። አራተኛው: (አልቀስሲይ) ከተልባ እግር (ከበፍታ) እና ከሐር ተቀላቅሎ የተሰራን ልብስ መልበስ ነው። አምስተኛው: የሐር ልብስ መልበስ ነው። ስድስተኛው: በወፍራም ሐር የተሰራን ልብስ መልበስ ነው። ሰባተኛው: ዲባጅ መልበስ ነው። እርሱም: ከሐር አይነቶች መካከል ምርጡና ውዱ ነው።