عَنْ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ يَنْهَاكُمْ أَنْ تَحْلِفُوا بِآبَائِكُمْ»، قَالَ عُمَرُ: فَوَاللهِ مَا حَلَفْتُ بِهَا مُنْذُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَهَى عَنْهَا ذَاكِرًا وَلَا آثِرًا.

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።' ዑመርም 'በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲከለክሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ራሴ በመናገርም ይሁን የሌላ ሰውን መሀላ ሳስተላልፍ በከለከሉት ምዬ አላውቅም።' አሉ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአባት መማልን እንደሚከለክል ተናገሩ። ስለዚህም መማል የፈለገ ሰው በአላህ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማል። ቀጥለውም ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲከለክሉ ከሰሙ ጀምሮ ሆን ብለውም ይሁን ሌላ ሰው ከአላህ ውጪ መማሉን በመናገር መልኩም ይሁን ምለው እንደማያውቁ አወሱ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከአላህ ውጪ በሆነ አካል መማል ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ሐዲሡ ላይ በአባት መማል ብቻ የመጣው የጃሂሊያዎች (የድንቁርና ዘመን ሰዎች) ልማድ ስለነበር ነው።
  2. ትክክለኛው መሀላ: አንድን ጉዳይ አፅንኦት ለመስጠት በአላህ ወይም በአላህ ስሞች ወይም በአላህ ባህሪያት መማል ነው።
  3. የዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል፤ ይህም የታዘዙትን በፍጥነት በመተግበራቸው፣ በጥሩ አረዳዳቸውና በጥንቁቅነታቸው ነው።