عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُما:
أَنَّ امْرَأَةً وُجِدَتْ فِي بَعْضِ مَغَازِي النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَقْتُولَةً، فَأَنْكَرَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَتْلَ النِّسَاءِ وَالصِّبْيَانِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3014]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
አንዲት ሴት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተሳተፉበት አንድ ጦርነት ላይ ተገድላ ተገኘች። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴትና ህፃናትን መግደልን አወገዙ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3014]
በአንድ ጦርነት ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዲት ሴት መገደሏን ተመለከቱ። እርሳቸውም የሴትንና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት መገደልን አወገዙ።