عَنِ ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما:
عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ نَهَى عَنِ النَّذْرِ، وَقَالَ: «إِنَّهُ لَا يَأْتِي بِخَيْرٍ، وَإِنَّمَا يُسْتَخْرَجُ بِهِ مِنَ الْبَخِيلِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1639]
المزيــد ...
ኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት:
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ‐ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ‐ ከስለት ከለከሉ። እንዲህም አሉ "እርሱ መልካምን ይዞ አይመጣም። በስለት የሚገኘው ትርፍ ስስታም ተገዶ ማውጣቱ ብቻ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1639]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከስለት ከለከሉ። ይህም አንድ ሰው አላህ ግዴታ ያላደረገበትን ነገር በራሱ ላይ ግዴታ ማድረጉ ማለት ነው። እንዲህም አሉ: ስለት አንድን ነገር አያመጣምም አያዘገይምም። ከስለት የሚገኘው ግዴታ የሆነበትን ነገር ካልሆነ በቀር የማይፈፅምን የሆነ ስስታም ሰው ተገዶ እንዲያወጣ ማስድረጉ ነው። ስለት ያልተወሰነልህን ነገር አያመጣም።