+ -

عَنْ أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ رضي الله عنه قَالَ:
أَتَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي رَهْطٍ مِنَ الأَشْعَرِيِّينَ أَسْتَحْمِلُهُ، فَقَالَ: «وَاللَّهِ لاَ أَحْمِلُكُمْ، مَا عِنْدِي مَا أَحْمِلُكُمْ» ثُمَّ لَبِثْنَا مَا شَاءَ اللَّهُ فَأُتِيَ بِإِبِلٍ، فَأَمَرَ لَنَا بِثَلاَثَةِ ذَوْدٍ، فَلَمَّا انْطَلَقْنَا قَالَ بَعْضُنَا لِبَعْضٍ: لاَ يُبَارِكُ اللَّهُ لَنَا، أَتَيْنَا رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَسْتَحْمِلُهُ فَحَلَفَ أَنْ لاَ يَحْمِلَنَا فَحَمَلَنَا، فَقَالَ أَبُو مُوسَى: فَأَتَيْنَا النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَذَكَرْنَا ذَلِكَ لَهُ، فَقَالَ: «مَا أَنَا حَمَلْتُكُمْ، بَلِ اللَّهُ حَمَلَكُمْ، إِنِّي وَاللَّهِ -إِنْ شَاءَ اللَّهُ- لا أَحْلِفُ عَلَى يَمِينٍ، فَأَرَى غَيْرَهَا خَيْرًا مِنْهَا، إِلَّا كَفَّرْتُ عَنْ يَمِينِي، وَأَتَيْتُ الَّذِي هُوَ خَيْرٌ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6718]
المزيــد ...

ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ከተወሰኑ የአሽዐር ተወላጆች ጋር በመሆን ለጂሀድ መጓጓዣ እንዲሰጡን ለመጠየቅ መጣሁ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "በአላህ እምላለሁ! መጓጓዣ አልሰጣችሁም። እኔ ዘንድ የምሰጣችሁ መጓጓዣ የለኝም።" ከዚያም አላህ የሻው ወቅት ያህል ቆየን። ግመል መጣላቸውና ለኛም ሶስት ግመል እንዲሰጠን አዘዙ። ግመሉን ይዘን ጉዞ የወጣን ጊዜ አንዳችን ለአንዳችን "አላህ በዚህ ግመል አይባርክልንና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የጂሀድ መጓጓዣ ግመል ፈልገን መጣን። እርሳቸውም መጓጓዣ እንደማይሰጡን ማሉና ቀጥሎ ሰጡን! (ለመሀላቸው ብለን መቀበል አልነበረብንም።)" ተባባልን።» አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት ይህንን አወሳንላቸው። እርሳቸውም "እኔ አይደለሁም መጓጓዣ የሰጠዋችሁ አላህ ነው የሰጣችሁ። እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንድ ጉዳይ ከማልኩ በኋላ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ከታየኝ የተሻለውን ፈፅሜ ለመሀላዬ ማካካሻ አደርጋለሁ እንጂ ከዚህ ውጪ ሌላ አላደርግም።" አሉን።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6718]

ትንታኔ

አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከተወሰኑ የጎሳዎቹ ሰዎች ጋር በመሆን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እንደመጡ ተናገሩ። የመምጣታቸው አላማም በጂሀድ ለመካፈል እንዲመቻቸው የሚጋልቡትን ግመል ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲሰጧቸው ለመጠየቅ ነው። እርሳቸውም መጓጓዣ እንደማይሰጧቸውና የሚሰጧቸው መጓጓዣም እንደሌላቸው ምለው ነገሯቸው። ተመለሱና የተወሰነ ጊዜ እንደቆዩ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ግመል መጣላቸው። ግመሎቹም ወደነርሱ ተላኩ። ከፊሎቹ ለከፊሉ: "አላህ በነዚህ ግመሎች ለኛ አይባርክልንና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጓጓዣ እንደማይሰጡን ምለው ሳለ እኛ እንዴት እንቀበላለን?" በመባባል መጥተው እርሳቸውን ጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: ለናንተ መጓጓዣውን የሰጣችሁ አላህ ነው። እርሱ ነው የገጠማችሁና የለገሳችሁ። እኔማ በእጃችሁ እንዲደርስ አማካኝ የሆንኩ ሰበብ ብቻ ነኝ። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንዳች የምሰራው ወይም በምተወው ነገር ላይ ምዬ ከዚያም ከዛ ከተማለለት ነገር ተቃራኒው የተሻለና በላጭ መሆኑን ካየው የተሻለውን ነገር ፈፅሜ የማልኩበትን ነገር እተወዋለሁ። ለመሀላዬም ማካካሻ አወጣለሁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الليتوانية الدرية الصربية الرومانية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ለወደፊት ለሚከሰት ነገር ቢሆንም እንኳ ንግግርን አፅንዖት ለመስጠት ሳያስምሉንም መማል እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  2. ከመሀላ በኋላ "ኢን ሻኣ አላህ" -በአላህ ፈቃድ- በሚል ቃል መሀላችንን የአላህ ፈቃድ ላይ ማንጠልጠል እንደሚፈቀድ፤ አላህ ከሻ የሚለውን ቃል ከመሀላው ጋር ነይቶ መሀላውን አስከትሎ የተናገረው መሀላውን ባፈረሰ ሰው ላይ ማካካሻ ግዴታ አይሆንም።
  3. ከተማለበት ነገር ይልቅ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ያገኘው ሰው መሀላውን ተቃርኖ ለመሀላው ማካካሻ በማውጣት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።