የሓዲሦች ዝርዝር

(ጎረቤቴን) ያስወርሰዋል ብዬ እስከማስብ ድረስ ጂብሪል በጎረቤት (ሐቅ ዙሪያ) እኔን ከማዘዝ አልተወገደም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንድ ጉዳይ ከማልኩ በኋላ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ከታየኝ የተሻለውን ፈፅሜ ለመሀላዬ ማካካሻ አደርጋለሁ እንጂ ከዚህ ውጪ ሌላ አላደርግም።" አሉን።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
‹ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ስንዴ በስንዴ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ገብስ በገብስ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ተምር በተምር መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው።›
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የወርቅና የብር ባለቤት ሆኖ ሐቃቸውን የማይወጣ ሰው የትንሳኤ ቀን ለርሱ የእሳት ዝርግ ተዘርግቶለት በርሷ በጀሃነም እሳት ውስጥ ሳይቃጠል የሚቀር የለም። ጎኑም፣ ግንባሩና ጀርባውም የሚተኮስ መሆኑ አይቀርም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።
عربي እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ