+ -

عَنِ الزُّبَيْرِ بْنِ العَوَّامِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَأَنْ يَأْخُذَ أَحَدُكُمْ حَبْلَهُ، فَيَأْتِيَ بِحُزْمَةِ الحَطَبِ عَلَى ظَهْرِهِ، فَيَبِيعَهَا، فَيَكُفَّ اللَّهُ بِهَا وَجْهَهُ خَيْرٌ لَهُ مِنْ أَنْ يَسْأَلَ النَّاسَ أَعْطَوْهُ أَوْ مَنَعُوهُ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1471]
المزيــد ...

ከዙበይር ቢን አልዓዋም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ሰዎች ሰጡትም ከለከሉት ሰዎችን ከሚለምን ይልቅ ገመዱን ይዞ በጀርባው እንጨት አስሮ እያመጣ በመሸጥ አላህ ፊቱን (ከመገረፍ) ቢጠብቅለት የተሻለ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1471]

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሰው ማንኛውንም ስራ መስራት እንዳለበትና ገመዱን ይዞ ጀርባው ላይ የሚሸከመውን እንጨት ሰብስቦ በገመዱ አስሮ በመሸጥ ካገኘው ገንዘብም መመገቡ ወይም መመፅወቱ ከሰዎችም መብቃቃቱና ከልመና ውርደት (በሰው ፊት ከመገረፍ) ፊቱን መጠበቁ ሰጡትም ከለከሉትም ሰዎችን ከመለመን የተሻለ እንደሆነ ገለፁ። ሰዎችን መለመን ውርደት ነው። አማኝ ደግሞ ቆፍጣና እንጂ ወራዳ አይደለም።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከመለመን በመጠበቅና ራስን ከልመና በማጥራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. አንድ ሰው በሰዎች እይታ ውዳቂና ቀላል የሚባል ሙያ ቢኖረው እንኳ ሲሳይን ለማግኘት ስራውን መስራቱ የሚበረታታ ጉዳይ እንደሆነ እንረዳለን።
  3. ኢስላም ልመናንና ስንፍናን የተዋጋ ሃይማኖት ነው። ለዚህም ሲባል እንደ እንጨት ለቀማ የመሰለ ከባድ ስራ እንኳ ቢሆን መልፋትንና መስራትን ግዴታ አድርጓል።
  4. ሲሳይ ለማግኘት መስራት እየቻሉ መለመን አይፈቀድም።
  5. አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አስተዳዳሪን መጠየቅ ይፈቀዳል። አላህ እንዲህ ብሏል {በእነዚያ ልትጭናቸው በመጡህ ጊዜ "በእርሱ ላይ የምጭናችሁ (አጋሰስ) አላገኝም።" ያልካቸው ስትሆን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው አይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ (የወቀሳ መንገድ የለባቸውም)።} [አት'ተውባህ: 92]
  6. ለመለመን የሚያስገድዱ ነገሮች ያጋጠሙት፣ መስራትና እንጨት ለቀማም ቢሆን የተሳነው ሰው ችክ ሳይል መለመን ይፈቀድለታል። አላህ እንዲህ ብሏል: {ሰዎችን በችክታ አይለምኑም።} [አልበቀራህ:273]
  7. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ የምንረዳው: ምፅዋት መስጠት፣ በላብ የተገኘን መብላትና ሐላል የሆኑ ስራዎችን መስራት የተበረታታ ጉዳይ እንደሆነ ነው።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ