عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ سمعتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يقولُ:
«أَلاَ إِنَّ الدُّنْيَا مَلْعُونَةٌ، مَلْعُونٌ مَا فِيهَا، إِلاَّ ذِكْرُ اللهِ وَمَا وَالاَهُ وَعَالِمٌ أَوْ مُتَعَلِّمٌ».
[حسن] - [رواه الترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 2322]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦
"አዋጅ! ዱንያ የተረገመች ናት። አላህን ማውሳት፣ አላህን ከማውሳት ጋር የተቆራኘ፣ ዐዋቂ (ዐሊም) ወይም ዕውቀት ፈላጊ ካልሆነ በቀር በዱንያ ውስጥ ያለውም የተረገመ ነው።"
[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2322]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህን ማውሳት፣ አላህን ወደ ማውሳት የቀረበና የተቆራኘ ወይም የሸሪዓን ዕውቀት ለሰዎች የሚያስተምር አዋቂ ወይም የሸሪዓን እውቀት የሚማር ካልሆነ በቀር ዱንያና በውስጧ ያሉ ነገሮች ባጠቃላይ ከአላህ የሚያጠምዱና የሚያርቁ ስለሆኑ በአላህ የተጠሉ፣ የተወገዙ፣ የተተዉና ከአላህ የራቁ እንደሆኑ ተናገሩ።