+ -

عَنِ ابْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَقِيتُ إِبْرَاهِيمَ لَيْلَةَ أُسْرِيَ بِي فَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ، أَقْرِئْ أُمَّتَكَ مِنِّي السَّلاَمَ، وَأَخْبِرْهُمْ أَنَّ الجَنَّةَ طَيِّبَةُ التُّرْبَةِ عَذْبَةُ الْمَاءِ، وَأَنَّهَا قِيعَانٌ، وَأَنَّ غِرَاسَهَا سُبْحَانَ اللهِ وَالحَمْدُ لِلَّهِ وَلاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَاللَّهُ أَكْبَرُ».

[حسن بشواهده] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 3462]
المزيــد ...

ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"እኔ ወደ ሰማይ ባረግኩበት ምሽት ኢብራሂምን አገኘኋቸው። እንዲህም አሉኝ ‹ሙሐመድ ሆይ! ለኡመትህ ከኔ የሆነን ሰላምታን አቅርብ! ጀነት ምርጥ አፈርና ጣፋጭ ውሃ እንዳላት ጀነት ገላጣ (ዛፍ የሌለባት) ሜዳ እንደሆነችና የሚተከልባትም ሱብሓነላህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር [በማለት] እንደሆነ ንገራቸው።›"»

[በማመሳከሪያዎቹ ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3462]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት የአላህ ፍፁም ወዳጅ የሆኑትን ኢብራሂምን ዐለይሂ ሰላም እንዳገኙ ተናገሩ። ለርሳቸውም «ሙሐመድ ሆይ! ለኡመትክ የኔን ሰላምታ አድርስ! ጀነት አፈሯ ምርጥና ውሃዋም ጨውነት የሌለው ጣፋጭ ውሃ እንደሆነ፤ ጀነት ዛፍ የሌለበት ቀጥ ያለና ሰፊ ሜዳ ሲሆን የጀነት ተክልም ምርጥ ንግግሮችና ቀሪ የሆኑ መልካም ስራዎች እንደሆኑ እነርሱም: "ሱብሓነላህ" "ወልሐምዱሊላህ" "ወላኢላሃ ኢለሏህ" "ወሏሁ አክበር" እንደሆኑና አንድ ሙስሊም በደጋገማቸው ቁጥር ጀነት ውስጥ ተክል እንደሚተከልለት ንገራቸው።» አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የጀነት ተክሎችን ለማብዛት ዚክርን በማዘውተር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ይህ ኢስላማዊው ማህበረሰብ የኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) ሰላምታ ስለተላከላቸው ደረጃቸውን ያስረዳናል።
  3. ኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) የሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡመት አላህን ማውሳት እንዲያበዙ ማነሳሳታቸውን እንረዳለን።
  4. ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "ጀነት ዛፍ የሌለባት ገላጣ ሜዳ ናት። ከዚያም ግን አላህ በችሮታው በሰሪዎች ስራ ልክ ጀነት ውስጥ ዛፎችንና ህንፃዎችን አስገኘ። ሁሉም ሰሪ በስራው ምክንያት እርሱ የተለየበት ፀጋ አለው። ከዚያም አላህ ሰውዬው ይህን ምንዳ እንዲያገኝ ለተፈጠረለት አላማ ስራውን ካገራለት በኋላ እነዚህ ዛፎችንም እንደሚተክል አደረገው።"