عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«لَيْسَ الْوَاصِلُ بِالْمُكَافِئِ، وَلَكِنِ الْوَاصِلُ الَّذِي إِذَا قُطِعَتْ رَحِمُهُ وَصَلَهَا».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 5991]
المزيــد ...
ከዐብደሏህ ቢን ዐምር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
"ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር ምላሹን የሚሰጥ የሆነው አይደለም፤ ይልቁንም ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል የሆነው ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5991]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እየነገሩን ያሉት ዝምድናን በመቀጠል የተሟላና ለዘመዶቹም በጎ ሰሪ የሚባለው ላደረጉለት መልካም ነገር መልካሙን በመመለስ ብቻ የተቆጠበ አይደለም። ይልቁንም ዝምድናውን በመቀጠል በኩል የተሟላ የሚባለው ዝምድናው በተቆረጠ ጊዜ የሚቀጥል፤ ሰዎቹ እያስከፉትም ለነርሱ መልካሙን በማድረግ ምላሽ የሚሰጣቸው የሆነ ነው።