عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«انْصُرْ أَخَاكَ ظَالِمًا أَوْ مَظْلُومًا». فَقَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَنْصُرُهُ إِذَا كَانَ مَظْلُومًا، أَفَرَأَيْتَ إِذَا كَانَ ظَالِمًا كَيْفَ أَنْصُرُهُ؟ قَالَ: « تَحْجُزُهُ -أَوْ تَمْنَعُهُ- مِنَ الظُّلْمِ؛ فَإِنَّ ذَلِكَ نَصْرُهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6952]
المزيــد ...
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"ወንድምህ በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እርዳው።" አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ተበዳይ የሆነ ጊዜ እረዳዋለሁ። እስኪ ንገሩኝ በዳይ በሆነ ጊዜ እንዴት ነው የምረዳው?" እርሳቸውም "ከመበደል ታቅበዋለህ ወይም ትከለክለዋለህ። ይህ እርሱን መርዳት ነው።" ብለው መለሱ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6952]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊም ወንድም በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እንዲረዳ አዘዙ። አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ተበዳይ በሆነ ጊዜ በደልን ከርሱ ላይ በማስወገድ እረዳዋለሁ። ንገሩኝ እስኪ በዳይ ከሆነ እንዴት ነው የምረዳው? እርሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ: ከበደል ትከለክለዋለህ፣ እጁን ትይዘዋለህ፣ ትገታዋለህ፣ ታቅበዋለህ። ይህ በሰይጣኑና በመጥፎ በምታዘው ነፍሱ ላይ እያገዝከው ነው።