عَنْ صَفْوَانَ بْنِ مُحْرِزٍ قَالَ: قَالَ رَجُلٌ لِابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما كَيْفَ سَمِعْتَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، يَقُولُ: فِي النَّجْوَى؟ قَالَ: سَمِعْتُهُ يَقُولُ:
«يُدْنَى الْمُؤْمِنُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مِنْ رَبِّهِ عَزَّ وَجَلَّ، حَتَّى يَضَعَ عَلَيْهِ كَنَفَهُ، فَيُقَرِّرُهُ بِذُنُوبِهِ، فَيَقُولُ: هَلْ تَعْرِفُ؟ فَيَقُولُ: أَيْ رَبِّ أَعْرِفُ، قَالَ: فَإِنِّي قَدْ سَتَرْتُهَا عَلَيْكَ فِي الدُّنْيَا، وَإِنِّي أَغْفِرُهَا لَكَ الْيَوْمَ، فَيُعْطَى صَحِيفَةَ حَسَنَاتِهِ، وَأَمَّا الْكُفَّارُ وَالْمُنَافِقُونَ، فَيُنَادَى بِهِمْ عَلَى رؤُوسِ الْخَلَائِقِ هَؤُلَاءِ الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَى اللهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2768]
المزيــد ...
ከሶፍዋን ቢን ሙሕሪዝ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ሰውዬ ለኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አለ: "የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለ መመሳጠር ሲናገሩ የሰማሀው ነገር አለን?" እርሱም አለ: "እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
‹አንድ አማኝ የትንሳኤ ቀን ወደ ጌታው ይቀርባል። በርሱ ላይ መሸፈኛውን አኑሮበት ወንጀሎቹን እንዲያምን ያደርገዋል። 'አወቅከውን?' ይለዋል። እርሱም 'ጌታዬ አውቄዋለሁ።' ይላል። አላህም 'እኔ በዱንያ ውስጥ ባንተ ላይ ሸፍኛት ነበር። ዛሬ ደግሞ ላንተ እምርሃለሁ።' ይለዋል። የመልካም ስራ መጽሐፉም ይሰጠዋል። ከሀዲዎችና ሙናፊቆች ግን በፍጡራን መካከል ይጠሩና 'እነዚህ በአላህ ላይ ያስተባበሉ ናቸው' ይባላሉ።›"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2768]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ አንድ አማኝ ባሪያውን የትንሳኤ ቀን እንደሚመሳጠረው እንዲህ በማለት ተናገሩ:
የትንሳኤ ቀን አማኝ የሆነ ሰው ወደ ጌታው ይቀርባል። ከርሱ ውጪ አንድም ሰው ምስጢሩን እንዳያውቅበትም ከቆሙ ሰዎች ይከልለዋል። እንዲህም ይለዋል:
"እንዲህ እንዲህ ... ወንጀልህን አወቅከው?" እያለ በባሪያውና በጌታው መካከል የሰራውን ወንጀሎች እንዲያረጋግጥ ያደርገዋል።
እርሱም "አዎ ጌታዬ" ይላል።
አማኙ የደነገጠና የፈራ ጊዜም አላህ ሱብሓነሁ እንዲህ ይለዋል: "ምድር ላይ ላንተ ሸፍኜልሃለሁ። ዛሬ ደግሞ ላንተ እምርሃለሁ።" የመልካም ስራ መጽሐፉም ይሰጠዋል።
ከሀዲና ሙናፊቅ ግን በፍጡራን መካከል እየተጠሩ እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹ ናቸው። አዋጅ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን ይባላሉ።