عَن أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يُسَلِّمُ الرَّاكِبُ عَلَى المَاشِي، وَالمَاشِي عَلَى القَاعِدِ، وَالقَلِيلُ عَلَى الكَثِيرِ».
وَلِلبُخَارِي: «يُسَلِّمُ الصَّغِيرُ عَلَى الكَبِيرِ، وَالمَارُّ عَلَى القَاعِدِ، وَالقَلِيلُ عَلَى الكَثِيرِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6232]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6232]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰዎች መካከል "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ" የሚለውን ሰላምታን የማቅረብ ስነ-ስርዓትን ጠቆሙ። ህፃን በትልቅ ላይ፣ ጋላቢ በእግረኛ ላይ፣ እግረኛ በተቀማጭ ላይ፣ ጥቂት ቁጥር ያላቸው በብዙዎቹ ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።