+ -

عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
أَلَسْتُمْ فِي طَعَامٍ وَشَرَابٍ مَا شِئْتُمْ؟ لَقَدْ رَأَيْتُ نَبِيَّكُمْ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَمَا يَجِدُ مِنَ الدَّقَلِ مَا يَمْلَأُ بِهِ بَطْنَهُ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2977]
المزيــد ...

ከኑዕማን ቢን በሺር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
"እናንተ የምትፈልጉትን ምግብና መጠጥ እየተመገባችሁ አይደልንዴ? ነቢያችሁን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሆዳቸውን የሚሞሉበት የሆነ የወረደ ተምርን እንኳ ሳያገኙ ቀርተው ተመልክቻቸዋለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2977]

ትንታኔ

ኑዕማን ቢን በሺር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሰዎች ያሉበት ፀጋ የፈለጉትን ያህል የሚበሉና የሚጠጡበት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልፀው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ግን ረሃባቸውን ለማስታገስ ሆዳቸውን የሚሞላ የወረደ ተምርን እንኳ የማያገኙበት ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ተናገረ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የነበሩበትን የዱንያ ዛሂድነት (ቸልተኝነት) መገለፁ።
  2. ከዱንያ ዛሂድ (ቸልተኛ) በመሆን፣ ዱንያን በማሳነስና ነቢዩን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመከተል ላይ መነሳሳቱን እንመለከታለን።
  3. ሰዎች ያሉበትን ፀጋ በማስታወስና አላህንም በማመስገን ላይ መተዋወስ እንደሚገባ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ