عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو رضي الله عنهما قَالَ: قالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«حَوْضِي مَسِيرَةُ شَهْرٍ، مَاؤُهُ أَبْيَضُ مِنَ اللَّبَنِ، وَرِيحُهُ أَطْيَبُ مِنَ المِسْكِ، وَكِيزَانُهُ كَنُجُومِ السَّمَاءِ، مَنْ شَرِبَ مِنْهَا فَلاَ يَظْمَأُ أَبَدًا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6579]
المزيــد ...
ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"የሐውዴ ( ኩሬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ፣ የብርጭቆዎቹ ብዛት የሰማያት ኮኮቦች ያህል ናቸው። ከሷ አንዴ የጠጣ ከቶም መቼም አይጠማም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6579]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የውመል ቂያማ የሚሰጣቸው ኩሬ እንዳለ እንዲሁም እርዝማኔውና ጎኑ አንድ ወር እንደሚያስኬድ ተናገሩ። ውኃው ከወተት እጅግ የበለጠ ንጣት እንዳለው፤ ሽታው ከሚስክ መአዛ የበለጠ ምርጥና ማራኪ መአዛ እንዳለው፤ የብርጭቆዎቹ ብዛት አምሳያ የሰማይ ኮኮቦች ያህል እንደሆነ፤ በዚህ ብርጭቆ ከኩሬው የጠጣ ሰው መቼም እንደማይጠማ ተናገሩ።