عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«يَقْبِضُ اللَّهُ الأَرْضَ، وَيَطْوِي السَّمَوَاتِ بِيَمِينِهِ، ثُمَّ يَقُولُ: أَنَا المَلِكُ، أَيْنَ مُلُوكُ الأَرْضِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4812]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4812]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን አላህ ምድርን እንደሚጨብጥና እንደሚሰበስባት፤ ሰማይንም ከፊሉን ከከፊሉ በላይ አድርጎ በቀኝ እጁ እንደሚጠቀልልና ገፍፎ እንደሚያጠፋቸው ከዚያም "እኔ ነኝ ንጉስ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!" እንደሚል ተናገሩ።