عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَتَقَارَبَ الزَّمَانُ، فَتَكُونَ السَّنَةُ كَالشَّهْرِ، وَيَكُونَ الشَّهْرُ كَالْجُمُعَةِ، وَتَكُونَ الْجُمُعَةُ كَالْيَوْمِ، وَيَكُونَ الْيَوْمُ كَالسَّاعَةِ، وَتَكُونَ السَّاعَةُ كَاحْتِرَاقِ السَّعَفَةِ الْخُوصَةُ».

[صحيح] - [رواه أحمد]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም። አመቱ እንደ ወር ይሆናል፤ ወሩ እንደ ሳምንት ይሆናል፤ ሳምንቱም እንደ ቀን ይሆናል፤ ቀኑም እንደ ሰአት ይሆናል፣ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠል እንደሚቃጠልበት ጊዜ (ያጠረ) ይሆናል።"

Sahih/Authentic. - [Ahmad]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰአቲቱ ምልክቶች መካከል አንዱ የጊዜ መቀራረብ መሆኑን ተናገሩ። ዓመቱ ልክ እንደ ወር ያልፋል፤ ወሩም ልክ እንደ ሳምንት ያልፋል፤ ሳምንቱም ልክ እንደ ቀን ያልፋል፤ ቀኑም ልክ አንድ ሰዓት እንደሚያልፈው ያልፋል፤ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠሉ በሚቃጠልበት ሀይለኛ ፍጥነት ልክ ቶሎ ያልፋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሰዓቲቱ ምልክቶች መካከል አንዱ የወቅት በረከት መነሳት ወይም ጊዜ መፍጠኑ ነው።