عَنْ جَابِرٍ رضي الله عنه قَالَ:
أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلٌ فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، مَا الْمُوجِبَتَانِ؟ فَقَالَ: «مَنْ مَاتَ لَا يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ، وَمَنْ مَاتَ يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا دَخَلَ النَّارَ»
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 93]
المزيــد ...
ጃቢር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦
ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ አንድ ሰውዬ በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሁለቱ (ጀነትና እሳት ውስጥ መግባትን) የሚያስወስኑ ነገሮች ምንድናቸው?" እሳቸውም "በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 93]
አንድ ሰውዬ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጀነት መግባትን ስለሚያስወስን እና እሳት መግባትን ስለሚያወስን ሁለት ነገሮች ጠየቃቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና፦ ጀነትን የሚያስወስነው ነገር ሰውዬው አላህን በብቸኝነት እያመለከ በሱ አንዳችንም ሳያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት። እሳትን የሚያስወስነው ነገር ደግሞ ሰውዬው ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ አምሳያ እና አቻ በማድረግ በአላህ ላይ አንዳችን ነገር እያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት።