عَنْ مُعَاذٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ:
كُنْتُ رِدْفَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى حِمَارٍ يُقَالُ لَهُ عُفَيْرٌ، فَقَالَ: «يَا مُعَاذُ، هَلْ تَدْرِي حَقَّ اللَّهِ عَلَى عِبَادِهِ، وَمَا حَقُّ العِبَادِ عَلَى اللَّهِ؟»، قُلْتُ: اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ، قَالَ: «فَإِنَّ حَقَّ اللَّهِ عَلَى العِبَادِ أَنْ يَعْبُدُوهُ وَلا يُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا، وَحَقَّ العِبَادِ عَلَى اللَّهِ أَنْ لا يُعَذِّبَ مَنْ لا يُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا»، فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ أَفَلاَ أُبَشِّرُ بِهِ النَّاسَ؟ قَالَ: «لا تُبَشِّرْهُمْ، فَيَتَّكِلُوا».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ሙዓዝ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ :
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኋላ ዑፈይር የሚባለው አህያ ላይ ተፈናጥጬ ሳለው "ሙዓዝ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅ፤ ባሮችስ አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ ታውቃለህን? " አሉ። "አላህና መልክተኛው ይወቁ !" አልኩኝ። እሳቸውም "አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች በአላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።" አሉ። "የአላህ መልክተኛ ሆይ ይህን ሰዎችን ላበስራቸውን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አታበስራቸው (በዚህ ስራ ብቻ) ይደገፋሉ (ይሳነፋሉ)። " አሉ።

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅና ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ አብራሩ። አላህ ባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ እሱን ብቻ ሊያመልኩና በሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ባሮች በአላህ ላይ ያላቸው ሀቅ ደግሞ እነዚያ በሱ ላይ አንዳችንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ያመለኩትን ላይቀጣ ነው። ቀጥሎ ሙዓዝ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎች በደስታ እንዲበሰሩ በዚህ የላቀ የአላህ ትሩፋት ላበስራቸውን?" አለ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሷ ላይ መደገፋቸውን ፈርተው እንዳያበስራቸው ከለከሉት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገው ሐቅ መገለፁ፤ እሱም፥ ሊያመልኩትና በሱ ላይም ምንንም ላያጋሩ መሆኑ።
  2. አላህ በችሮታውና በፀጋው በነፍሱ ላይ ግዴታ ያደረገው የባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ መገለፁ፤ እሱም ጀነት ሊያስገባቸውና ላይቀጣቸው ነው።
  3. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ አላህ ላይ አንዳችንም የማያጋሩ የተውሒድ ሰዎች መመለሻቸው ጀነት መሆኑን የሚገልፅ ትልቅ ብስራት አለ።
  4. ሙዓዝ ዕውቀት በመደበቃቸው ወንጀል ውስጥ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ይህን ሐዲሥ የተናገሩት ከመሞታቸው በፊት (ወደ ሞት አፋፍ ሲቃረቡ) ነው።
  5. አንዳንድ ሐዲሦችን ከፊል ሰዎች ትርጉሙን በአግባቡ አይረዱትም ተብሎ ከተሰጋ አለመናገርን ያስገነዝበናል። ይህ የማንነግራቸው ግን በሐዲሡ ስር ተግባርን የሚያዝና ሸሪዐዊ የቅጣት ብይኖችን የሚያስቀምጥ ሐዲሥ ካልሆነ ነው።
  6. ከተውሒድ ሰዎች መካከል ወንጀል የሰሩ በአላህ ፍላጎት ስር መሆናቸው። ከፈለገ የሚቀጣቸው፤ ከፈለገም የሚምራቸው እነደሆነ እና መመለሻቸው ወደ ጀነት መሆኑን።