عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَالَ:
جَاءَ رَجُلٌ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، مَا تَرَكْتُ حَاجَّةً وَلَا دَاجَّةً إِلَّا قَدْ أَتَيْتُ، قَالَ: «أَلَيْسَ تَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ؟» ثَلَاثَ مَرَّاتٍ. قَالَ: نَعَمْ، قَالَ: «فَإِنَّ ذَلِكَ يَأْتِي عَلَى ذَلِكَ».

[صحيح] - [رواه أبو يعلى والطبراني والضياء المقدسي]
المزيــد ...

አነስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦
አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት " የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንጀል ትንሽም ሆነ ትልቅ የሰራሁት ቢሆን እንጂ አልተውኩትም! " አለ። እርሳቸውም "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?" በማለት ሶስት ጊዜ ጠየቁት። እርሱም "አዎን" አለ። እሳቸውም "ይህ ምስክርህ በነዛ ወንጀሎችህ ላይ ያልፋሉ (ወንጀሎችህን ያብሳቸዋል)" አሉት።

Sahih/Authentic. - [Abu Ya‘laa]

ትንታኔ

አንድ ሰው ወደ ነቢዩየአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሁሉንም ዓይነት ወንጀሎችና ኃጢኣቶች ሰርቻለሁ፤ ትንሽም ሆነ ትልቅ ወንጀል ከመስራት አልተቆጠብኩም፤ ምህረት ይደረግልኝ ይሆን?" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሱ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?" አሉት። ሶስት ጊዜ ደጋግመው ጠየቁት። እርሱም፦ "አዎን እመሰክራለሁ" በማለት መለሰላቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሁለቱ የምስክር ቃላቶች ትሩፋትና ወንጀል የማስማር አቅማቸው እንደሚማር ነገሩት። ተውበት ያለፈውን ወንጀል ያብሳልና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሁለቱ ምስክር ቃላት ታላቅነትና እውነተኛ በሆነ ልቡም የተናገራት ጊዜ ወንጀሎች ላይ የሚኖራት የበላይነት።
  2. እስልምና ያለፈን ወንጀል የሚያብስ (የሚያስምር) መሆኑን።
  3. እውነተኛ ተውበት (ጸጸት) ያለፈን ወንጀል የምታብስ መሆኑን።
  4. በማስተማር ሂደት ውስጥ መደጋገም ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ፈለግ መካከል መሆኑን።
  5. የሁለቱ ምስክር ቃላቶች ትሩፋት፥ እሳት ውስጥ ከመዘውተር ለመዳን ሰበብ መሆናቸው።