عَنْ سُفْيان بنِ عَبْدِ اللهِ الثَّقَفِيّ رضي الله عنه قال:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ، قُلْ لِي فِي الْإِسْلَامِ قَوْلًا لَا أَسْأَلُ عَنْهُ أَحَدًا غَيْرَكَ، قَالَ: «قُلْ: آمَنْتُ بِاللهِ، ثُمَّ اسْتَقِمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم وأحمد]
المزيــد ...

ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ሶሐቢዩ ሱፍያን ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ ስለርሱ አንድንም ሳይጠይቅ እርሱን አጥብቆ የሚይዘው የሆነን የኢስላምን ሀሳቦች የጠቀለለ የሆነን ንግግር እንዲያስተምሩት ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠየቀ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "አላህ ብቻውን ጌታዬ፣ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ፣ አጋር የሌለው በእውነት የሚመለከው ብቸኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ። በል!" አሉት። ከዚያም ለአላህ ትእዛዝ የአላህን ግዴታዎች በመፈፀምና የአላህን ክልከላዎች በመተው ታዛዥ ይሁን፤ በርሱ ላይም ይዘውትር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሃይማኖቱ መሰረት በአላህ ጌትነት፣ ተመላኪነትና በስምና ባህሪያቶቹ ማመን ነው።
  2. ከማመን በኋላ ቀጥ የማለትን፣ በአምልኮ ላይ የመዘውተርና በዚህም ላይ የመፅናትን አንገብጋቢነት እንረዳለን።
  3. ኢማን ሥራዎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው መስፈርት ነው።
  4. በአላህ ማመን ሲባል ማመን ግዴታ የሚሆንባቸውን እምነታዊ ጎዳዮችና መሰረቶችን፣ ይህንንም ተከትለው የሚመጡ የቀልብ ተግባራትን፣ በውስጥም ይሁን በውጪ ታዛዥነትንና እጅ መስጠትን ያጠቃልላል።
  5. "ኢስቲቃማ" (ቀጥ ማለት) ሲባል ግዴታዎችን በመስራትና ክልክሎችን በመተው ቀጥተንኛውን ጎዳና አጥብቆ መያዝ ማለት ነው።
ተጨማሪ