عَنِ ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَ:
«مَثَلُ الْمُنَافِقِ، كَمَثَلِ الشَّاةِ الْعَائِرَةِ بَيْنَ الْغَنَمَيْنِ تَعِيرُ إِلَى هَذِهِ مَرَّةً وَإِلَى هَذِهِ مَرَّةً».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የሙናፊቅን ሁኔታ ከሁለት የፍየል መንጋ የትኛውን የፍየል መንጋ መከተል እንዳለባት እንዳላወቀች አንድ ፍየል አምሳያ እንደሆነ ገለፁ። ወደዛ መንጋ አንዴ ትሄዳለች ወደሌላኛው ደግሞ ሌላ ጊዜ ትሄዳለች። እነሱም በኢማንና ክህደት መካከል የዋለሉ ናቸው። በውጫዊና ውስጣዊ ማንነታቸው ከአማኞችም ጋር አይደሉም ከከሀዲዎችም ጋር አይደሉም። በተቃራኒ ውጫቸው ከአማኞች ጋር ሲሆን ውስጣቸው በጥርጣሬና ማወላወል የተሞላ ነው። ልባቸው አንዳንዴ ወደ አማኞች ሲዘነበል አንዳንዴ ደግሞ ወደከሀዲያን ይዘነበላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቀና ጎዳና መሀል የተፈለገውን ሀሳብ በደንብ እንዲረዱት ምሳሌ መጥቀስ አንዱ ነው።
  2. ሙናፊቆች ያለባቸውን የማወላወል፣ የጥርጣሬና አለመረጋጋት ባህሪ መገለፁ።
  3. ከሙናፊቆች መገለጫ መጠንቀቅ እንዲሁም በውጫዊም ሆነ በውስጣዊ እምነታችን ቆራጥና እውነተኛ መሆን እንዳለብን መነሳሳቱ።