عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رضي الله عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ الْإِيمَانَ لَيَخْلَقُ فِي جَوْفِ أَحَدِكُمْ كَمَا يَخْلَقُ الثَّوْبُ الْخَلِقُ، فَاسْأَلُوا اللَّهَ أَنْ يُجَدِّدَ الْإِيمَانَ فِي قُلُوبِكُمْ».

[صحيح] - [رواه الحاكم والطبراني] - [المستدرك على الصحيحين: 5]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሓኪምና ጦበራኒይ ዘግበውታል።] - [አልሙስተድረክ ዓለስሶሒሐይን - 5]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አዲስ ልብስን ለረጅም ጊዜ በመገልገላችን ምክንያት እንደሚደክም ሁሉ ኢማንም በሙስሊም ቀልብ ውስጥ እንደሚደክምና እንደሚያረጅ ተናገሩ። ይህም አምልኮ መፈፀምን በማቋረጥ ወይም ወንጀልን በመፈፀምና በስሜት ውስጥ በመዘፈቅ ምክንያት ነው። ስለዚህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ግዴታ ነገሮችን በመፈፀም፣ ውዳሴና ምህረት መለመንን በማብዛት አላህ ኢማናችንን እንዲያድስልን እንድንለምነው ጠቆሙን።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ፅናት እንዲሰጠንና በቀልባችን ውስጥ ኢማንን እንዲያድስልን አላህን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ኢማን ንግግርም ተግባርም እምነትም ሲሆን በአምልኮ (የአላህን ትዕዛዛት በመፈፀም) ሲጨምር በወንጀል ደግሞ ይቀንሳል።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (65)
ተጨማሪ