+ -

عَنْ أَنَسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ: لَأُحَدِّثَنَّكُمْ حَدِيثًا سَمِعْتُهُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لاَ يُحَدِّثُكُمْ بِهِ أَحَدٌ غَيْرِي: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِنَّ مِنْ أَشْرَاطِ السَّاعَةِ أَنْ يُرْفَعَ العِلْمُ، وَيَكْثُرَ الجَهْلُ، وَيَكْثُرَ الزِّنَا، وَيَكْثُرَ شُرْبُ الخَمْرِ، وَيَقِلَّ الرِّجَالُ، وَيَكْثُرَ النِّسَاءُ حَتَّى يَكُونَ لِخَمْسِينَ امْرَأَةً القَيِّمُ الوَاحِدُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5231]
المزيــد ...

አነስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ "ከኔ ውጪ ማንም የማይነግራችሁን ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የሰማሁትን አንድ ሐዲሥ እነግራቹሀለሁ። የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
"ከሰዓቲቱ (ቂያማ) ምልክቶች መካከል ዕውቀት ይነሳል፣ መሀይምነት ይስፋፋል፣ ዝሙት ይበረክታል፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ይበዛል፣ ለሀምሳ ሴቶች አንድ (ወንድ) አስተዳዳሪ እስኪሆን ድረስ ወንዶች አንሰው ሴቶች ይበዛሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5231]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የቂያማን መቅረብ ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል የሸሪዐ ዕውቀት መነሳቱን ገለፁ። ይህም የሚሆነው ዑለሞች በመሞታቸው ነው። የዚህም ውጤት የመሀይምነት መሰራጨትና መብዛትን፣ የፀያፍ ድርጊቶችና ዝሙት መስፋፋትን፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት መብዛትን ያስከትላል። ለሀምሳ ሴቶች ጉዳይ የሚያስፈፅመውና የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማሟላት ኃላፊነት የሚወስደው አንድ ወንድ እስኪሆን ድረስ የወንዶች ቁጥር ሲመነምን የሴቶች ቁጥር ደግሞ ይጨምራል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጥቂት የቂያማ ምልክቶች መገለፃቸው።
  2. ቂያማ የምትከሰትበትን ወቅት ማወቅ አላህ የተነጠለበት ከሆኑ የሩቅ ዕውቀቶቹ መካከል አንዱ ነው።
  3. ሸሪዐዊ ዕውቀትን ከመጥፋቱ በፊት መማር እንደሚገባ መነሳሳቱ (መበረታታቱ)።
ተጨማሪ