عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَمُرَّ الرَّجُلُ بِقَبْرِ الرَّجُلِ فَيَقُولُ: يَا لَيْتَنِي مَكَانَهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 7115]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7115]

ማብራሪያ

ሰውዬው በቀብር በኩል እያለፈ ሞቶ በተቀበረው ፋንታ ሞቶ በነበር እስኪመኝ ድረስ ሰአቲቱ እንደማትቆም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። የዚህ ምክንያትም ጥመትና የጥመት ባለቤቶች በመብዛታቸው፣ ፈተና፣ ወንጀልና ውግዝ ተግባራት ይፋ በመሆናቸው ሳቢያ ኢማኑ እንዳይጠፋ በነፍሱ ላይ በመፍራቱ ነው።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. በመጨረሻው ዘመን ወንጀሎችና ፈተናዎች ይፋ እንደሚሆኑ መጠቆሙን እንረዳለን።
  2. ጥንቃቄ በማድረግ፣ በኢማንና በመልካም ስራ ለሞት መዘጋጀት እና ከፈተናና መከራ ስፍራዎች መራቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (56)