عَنِ ابْنِ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ:
قَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللهِ، أَنُؤَاخَذُ بِمَا عَمِلْنَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ؟ قَالَ: «مَنْ أَحْسَنَ فِي الْإِسْلَامِ لَمْ يُؤَاخَذْ بِمَا عَمِلَ فِي الْجَاهِلِيَّةِ، وَمَنْ أَسَاءَ فِي الْإِسْلَامِ أُخِذَ بِالْأَوَّلِ وَالْآخِرِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6921]
المزيــد ...

ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡-
“አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6921]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት አብራሩ። እስልምናውን አሳምሮ፣ እውነተኛና ሙኽሊስ (ያጠራ) ሆኖ የሰለመ ሰው ከመስለሙ በፊት በሠራው ወንጀል አይጠየቅም። ወደ እስልምና ከገባ በኋላ ሙናፊቅ በመሆን ወይም ከእምነቱ በመውጣት መጥፎ የሠራ ግን በክህደት ዘመኑም ሆነ በእስልምና ዘመኑ ስለ ሠራው ሥራ ይጠየቃል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በጃሂሊያ ዘመን ለሰሩት ስራ የሰጡት ትኩረትና ፍርሃታቸውን እንረዳለን።
  2. በእስልምና ላይ መፅናት መበረታታቱን እንረዳለን።
  3. ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት እንረዳለን። እሱም ያለፈውን መጥፎ ስራዎች ማስማሩ ነው።
  4. ከእስልምና የወጣና ሙናፊቅ የሆነ ሰው ቀደም ብሎ ከመስለሙ በፊት ስለ ሠራቸው ሁሉ ሥራዎችና በእስልምና ውስጥም ስለ ሰራቸው ሁሉ ወንጀሎች ይጠየቃል።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (66)
ተጨማሪ