የሐዲሦች ዝርዝር

'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው።
عربي الإنجليزية الأوردية
ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።
عربي الإنجليزية الأوردية
የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል።
عربي الإنجليزية الأوردية
አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት።
عربي الإنجليزية الأوردية
ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
عربي الإنجليزية الأوردية
አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።
عربي الإنجليزية الأوردية
ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።
عربي الإنجليزية الأوردية
በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት እና በነቢዩ ሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።
عربي الإنجليزية الأوردية