عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«المُسْلِمُ مَنْ سَلِمَ المُسْلِمُونَ مِنْ لِسَانِهِ وَيَدِهِ، وَالمُهَاجِرُ مَنْ هَجَرَ مَا نَهَى اللَّهُ عَنْهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 10]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው፤ ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 10]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስልምናው የተሟላ ሙስሊም የሚባለው ሙስሊሞች ከምላሱ ሰላም የሆኑበት ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ስለዚህም አይሰድባቸውምም፤ አይረግማቸውምም፤ አያማቸውምም፤ በሙስሊሞች መካከል በምላስ ከሚመጡ ማናቸውም የክፋት አይነት በየትኛውም ሊጎዳቸው አይሮጥም። ከእጁም ሙስሊሞች ሰላም የሆኑበት ነው። ስለዚህም በነርሱ ላይ ወሰን አያልፍም፤ ያለ አግባብ ገንዘባቸውን አይወስድምም በሌሎች መሰል ሁኔታዎችም ሙስሊሞችን አይጎዳም። ሙሃጂር ማለት: አላህ ክልክል ያደረገውን የተወ ነው።