عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَ:
«إِذَا جَاءَ رَمَضَانُ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ النَّارِ، وَصُفِّدَتِ الشَّيَاطِينُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1079]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1079]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዷን ወር የገባ ጊዜ ሶስት ነገሮች እንደሚከሰቱ ተናገሩ:- አንደኛ: የጀነት በሮች ይከፈታሉ። ከጀነት በሮችም አንድም በር አይዘጋም። ሁለተኛ: የእሳት በሮች ይዘጋሉ። አንድም የእሳት በር አይከፈትም። ሶስተኛ: ሰይጣኖችና አመፀኛ ጋኔኖች በሰንሰለት ይጠፈነጋሉ። ከረመዷን ውጪ ይደርሱበት ወደነበረው አይደርሱም። ይህ ሁሉ ለዚህ ወር ልቅና፣ ከሶላት፣ ከሶደቃ፣ ከዚክር፣ ቁርአን ከመቅራትና ከዛም ውጪ ያሉ አምልኮዎች በማብዛት ላይና ከወንጀሎችና ከሀጢአቶች በመራቅ ላይ ሰሪዎችን ለማነሳሳት ነው።