عَنْ عَائِشَةَ رضي الله عنها قَالَتْ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الْمَاهِرُ بِالْقُرْآنِ مَعَ السَّفَرَةِ الْكِرَامِ الْبَرَرَةِ، وَالَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَتَتَعْتَعُ فِيهِ، وَهُوَ عَلَيْهِ شَاقٌّ، لَهُ أَجْرَانِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 798]
المزيــد ...
ከዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና -እንደተላለፈው፡ "የአሏህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፡
"ቁርአንን አሳምሮ የሚያነብ ሰው የተከበሩና ታዛዥ ከሆኑ መላዕክቶች ጋር ነው፤ ቁርኣንን ሲያነብ ከብዶት እየተቸገረ የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ አለው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 798]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን ሽምደዳውን አሳምሮ፤ አስተማማኝ በሆነ መልኩ፤ ውብና ቆንጆ አድርጎ የሚያነብ ሰው በመጪው ዓለም ያለው ምንዳ ደረጃው ታዛዥና የተከበሩ ከሆኑ መላእክቶች ጋር እንደሆነ፤ ቁርአንን የመሸምደድ አቅሙ ደካማ ስለሆነ ቁርአን ማንበብ በርሱ ላይ ከባድና አስቸጋሪ ሆኖበት እየተንተባተበና እየመላለሰ የሚያነብ ከመሆኑም ጋር ሳያቋርጥ ዘውትር የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ እንዳለው ተናገሩ። አንዱ ምንዳ የማንበቡ ምንዳ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የመላለሰበትና ተቸግሮ የማንበቡ ምንዳ ነው።