عَنْ مُعَاوِيَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«الْمُؤَذِّنُونَ أَطْوَلُ النَّاسِ أَعْنَاقًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 387]
المزيــد ...
ከሙዓዊያህ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"አዛን አድራጊዎች የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 387]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለሶላት የሚጣሩ አዛን አድራጊዎች ስራቸው የላቀ፣ መልካማቸው የበዛና ምንዳቸው የገዘፈ በመሆኑ የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ አንገተ ረጃጅሞች እንደሚሆኑ ተናገሩ።