عَنْ سَهْلٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ فِي الْجَنَّةِ بَابًا يُقَالُ لَهُ الرَّيَّانُ، يَدْخُلُ مِنْهُ الصَّائِمُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، لَا يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، يُقَالُ: أَيْنَ الصَّائِمُونَ، فَيَقُومُونَ لَا يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، فَإِذَا دَخَلُوا أُغْلِقَ، فَلَمْ يَدْخُلْ مِنْهُ أَحَدٌ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1896]
المزيــد ...
ከሰህል ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
«ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። "ጾመኞች የት አሉ?" ይባላል። እነርሱም ይቆማሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። እነርሱ የገቡ ጊዜ ይዘጋል። በርሱ በኩል ማንም አይገባም።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1896]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከጀነት በሮች መካከል "የረያን በር" ተብሎ የሚጠራ በር እንዳለና የትንሳኤ ቀን በርሱ በኩል ጾመኞች እንደሚገቡበት ተናገሩ። ከነርሱ ውጪም በርሱ በኩል አንድም ሰው እንደማይገባበት፤ "ጾመኞች የት አሉ?" ተብሎም እንደሚለፈፍ፤ ጾመኞችም ተነስተው እንደሚገቡ፤ በርሱ በኩል ከነርሱ ውጪ ማንም እንደማይገባበት፤ የመጨረሻቸው ሰው ከገባ በኃላ እንደሚዘጋና ከዛ በኋላም በርሱ በኩል ማንም እንደማይገባበት ተናገሩ።