عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ»
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 38]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 38]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የረመዳንን ወር በአላህ አምኖ፣ በፆም ግዴታነትና አላህ ለፆመኞች ያዘጋጀውን የደለበ ምንዳና አጅር እውነት ብሎ እንዲሁም ፆሙም ለይዩልኝና ይስሙልኝ ሳይሆን የአላህን ፊት ፈልጎበት የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉን እንደሚማር ነገሩን።