عَنْ أَبَي قَتَادَةَ رضي الله عنه أنَّهُ طَلَبَ غَرِيمًا لَهُ، فَتَوَارَى عَنْهُ ثُمَّ وَجَدَهُ، فَقَالَ: إِنِّي مُعْسِرٌ، فَقَالَ: آللَّهِ؟ قَالَ: آللَّهِ؟ قَالَ: فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَنْ سَرَّهُ أَنْ يُنْجِيَهُ اللهُ مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ فَلْيُنَفِّسْ عَنْ مُعْسِرٍ أَوْ يَضَعْ عَنْهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1563]
المزيــد ...
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አቡ ቀታዳህ አንድ ተበዳሪውን ሲፈልገው ከርሱ ተሸሸገ። ከዚያም አገኘው። ተበዳሪውም "እኔ ችግርተኛ ነኝ።" አለው። እርሱም "ወላሂ በል!" አለው። ተበዳሪውም "ወሏሂ!" አለ። አቡቀታዳም እንዲህ አለ: "እኔ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:‐
‹‹ከትንሳኤ ቀን ችግሮች አላህ እንዲገላግለው ያስደሰተው ሰው ለችግርተኛ ፋታ ይስጥ ወይም ከርሱ ያቅልልለት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1563]
አቡቀታዳህ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከርሱ ይደበቅ የነበረን ተበዳሪን ይፈልግ ነበርና አገኘው። ተበዳሪውም እንዲህ አለው "እኔ ችግርተኛ ነኝ። እዳህን የምከፍልበት ገንዘብም የለኝም።"
አቡቀታዳህም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ገንዘብ እንደሌለው ምሎ እንዲነግረው ጠየቀው።
በሚናገረው ነገር እውነቱን እንደሆነም በአላህ ምሎ ነገረው።
አቡ ቀታዳህም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ እነደደሰማ ተናገረ:
አላህ ከትንሳኤ ቀን ችግሮችና ጭንቆች እንዲያድነው ያስደሰተው ሰው ከችግርተኛ ያቅልል። ይህም መክፈያ ጊዜውን በማዘግየትና በማርዘም ወይም የተወሰነውን እዳ ወይም ሁሉንም ይቅር በማለት ነው።