عن أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ رضي الله عنه: أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«مَنْ صَلَّى الْبَرْدَيْنِ دَخَلَ الْجَنَّةَ»
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 574]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡
"ሁለቱን ቀዝቃዛ ወቅቶች ሶላት የሰገደ ሰው ጀነት ገባ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 574]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሁለቱን ቀዝቃዛ ወቅቶች ሶላት ለመስገድ በመጣር ላይ አነሳሱ። እነሱም: የፈጅርና የዐስር ሶላቶች ናቸው። በጊዜው፣ በጀመዓና ሌሎቹንም የሶላት ሐቆች አሟልቶ እነዚህን ሶላቶች የሰገደ ሰውን ጀነት መግቢያ ሰበብ እንደሚሆኑት በመንገር አበሰሩ።