عن جُندب بن عبد الله القَسْرِِي رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ صَلَّى صَلَاةَ الصُّبْحِ فَهُوَ فِي ذِمَّةِ اللهِ، فَلَا يَطْلُبَنَّكُمُ اللهُ مِنْ ذِمَّتِهِ بِشَيْءٍ، فَإِنَّهُ مَنْ يَطْلُبْهُ مِنْ ذِمَّتِهِ بِشَيْءٍ يُدْرِكْهُ، ثُمَّ يَكُبَّهُ عَلَى وَجْهِهِ فِي نَارِ جَهَنَّمَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 657]
المزيــد ...
ከጁንዱብ ቢን ዐብደላህ አልቀስሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው። ከናንተ አንዳችሁ በአላህ ጥበቃ ስር ያለውን ሰው በምንም መንገድ አይጉዳ። ያንን የሠራ ሰው የአላህ ቁጣ በእርግጥ ይይዘዋል ከዚያም በአፍጢሙ በጀሀነም እሳት ውስጥ ይደፋዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 657]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃና ከለላ ስር ስላለ እንደሚከላከልለትና እንደሚረዳው ተናገሩ።
ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት በመተው ወይም ሰጋጁን በመተናኮልና ሰጋጁ ላይ ወሰን በማለፍ ይህንን ከለላ ከማፍረስ አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመም ይህንን ጥበቃ ስለጣሰ ለብርቱ ዛቻ የተጋለጠ ይሆናል። የአላህን ሀቅ ወሰን ስላለፈም በአላህ ይፈለጋል። አላህም የሚፈልገውን ያገኘዋል፤ ከዚያም በአፍጢሙ እሳት ውስጥ ይደፋዋል።