+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ تَوَضَّأَ فَأَحْسَنَ الْوُضُوءَ ثُمَّ أَتَى الْجُمُعَةَ فَاسْتَمَعَ وَأَنْصَتَ غُفِرَ لَهُ مَا بَيْنَهُ وَبَيْنَ الْجُمُعَةِ وَزِيَادَةُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ، وَمَنْ مَسَّ الْحَصَى فَقَدْ لَغَا».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 857]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ዉዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ ጁሙዓ በመምጣት ኹጥባን ዝም ብሎ ያዳመጠ በዚህኛው ጁሙዓና በቀጣዩ ጁሙዓ መካከል የሰራው ተጨማሪም ሶስት ቀን የሰራው ወንጀል ይማራል። ጠጠርን የነካካ በርግጥም (የጁመዓውን ምንዳ) ውድቅ አድርጓል።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 857]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያሉት: ዉዱእን ማዕዘናቶቹን አሟልቶ፣ ሱናዎቹንና ስነስርአቶቹንም በመፈፀም አሳምሮ ካደረገ በኃላ ወደ ጁሙዓ ሶላት በመምጣት ዝም ብሎ ኹጥባውን ያዳመጠና ከዛዛታ ነገር ዝም ያለ ሰው አላህ ለርሱ የአስር ቀን ትናንሽ ወንጀሎቹን ይምረዋል። እነሱም ከሰገደው ጁሙዓ ቀን እስከሚቀጥለው ጁሙዓ ድረስና የተጨማሪ ሶስት ቀን ወንጀል ነው። ምክንያቱም መልካም ስራ አስር አምሳያውን ያስመነዳልና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኹጥባ ላይ ለሚነገረው ተግሳፅ የልብን ትኩረት ከመንፈግ፣ በሰውነት ከመጫወት፣ ጠጠርን በመነካካትና በሌሎችም በሚጠምዱ የጨዋታ አይነቶች ከመዘናጋት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ በርግጥም የጁሙዓውን የተሟላ ስራ ውድቅ አድርጎታል። ውድቅ ስራ የሰራ ሰውም ከተሟላ የጁሙዓ ምንዳ ለርሱ ድርሻ የለውም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዉዱእን በመፈፀም ላይ፣ በተሟላ መልኩ በማሟላት ላይና የጁሙዓ ሶላትን መጠባበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. የጁመዓ ሶላት ትሩፋትን እንረዳለን።
  3. ለጁሙዓ ኹጥባ ዝም ማለት፣ ከጁሙዓ ኹጥባ በማውራትና በሌላም ተግባር ከመጠመድ መጠንቀቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  4. በኹጥባ መሀል ውድቅ ተግባር የሰራ ሰው ምንዳው ከመጉደሉም ጋር የጁሙዓ ሶላቱ የሚያብቃቃውና ግዴታውን የሚያነሳለት ነው።